Thursday, April 17, 2014

በዘለሊሁ ፈቀደ... ወበዘውእቱ ሠምረ...

አገበረቶ ኂሩቱ ከመ ይሕምም በእንቲአነ፤ 
ወፍቅረ እጓለመሕያው ሰሐበቶ ከመ ይስተይ ጽዋዐ ሞት በእንተ ኀጣውኢነ። 
ስለኛ ይታመም ዘንድ ቸርነቱ አስገደደቺው፤
ስለኀጢአታችንም የሞትን ጽዋ ይጠጣ ዘንድ የሰው ፍቅር ሳበቺው።
...
ንበልኬ እንከሰ፦
በዘለሊሁ ፈቀደ አሕመምዎ...
ወበዘውእቱ ሠምረ ጥዕመ ሞተ በሥጋ። 
በዘለሊሁ ፈቀደ ነበረ ውስተ ከርሠ መቃብር ሠሉሰ መዋዕለ ወሠሉሰ ለያልየ...
ወበዘውእቱ ሠምረ ሦጣ ለነፍሱ ውስተ ሥጋሁ ወተንሥአ በኀይለ መለኮቱ። 
እንግዴኽስ  እንዲኽ እንበል፦
ራሱ በፈቀደ ገንዘብ ሕማምን ተቀበለ...
ርሱው በወደደ ገንዘብ ሞትን ቀመሰ።
ራሱ በፈቀደ ገንዘብ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐደረ...
ርሱው በወደደ ገንዘብ ነፍሱን ከሥጋው አዋሕዶ በመለኮቱ ኀይል ተነሣ። 
[አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ]  
 እንኳን ለበዓለ ስቅለቱ ወትንሣኤሁ በሰላም አደርሳችኍ አደረሰን!

Sunday, January 19, 2014

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችኍ፤ አደረሰን!

ውስተ ባሕር ፍኖትከ
ወአሠርከኒ ውስተ ማይ ብዙኅ
ጎዳናኽ በዮርዳኖስ ተገለጸ
ወንጌልኽ በዚኽ ዓለም ተነገረ።
(መዝ 76፡19)
[የዘይቤ ሳይኾን፤ የምስጢር ትርጕም ነው!]
በዐበይት በዓላትና በመሳሰለው ዅሉ መልካም ምኞትን ለመግለጥ የምንጠቀምባቸውን ትውፊት-ወረድ ኀይለ ቃሎች ልብ ማለት ይገባል። ስለ "እንኳን..." ከዚኽ ቀደም ተናግረናል። አኹን ደግሞ እስኪ ስለ "ብርሃነ..." አጭር ነገር እንጠቍም፦

"እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ/ልደቱ/ጥምቀቱ/ትንሣኤው አደረሳችኍ እንላለን። ለዚኽም መሠረታችን ቅዱሳት መጻሕፍት ናቸው፦ "ወንዜንወክሙ ከመ እግዚአብሔር ብርሃን ውእቱ..." (1ኛ ዮሐ 1፡5) "እስመ ብርሃን መጽአ ውስተ ዓለም..." (ዮሐ 3፡19) ወእለተርፉ/ወዘተርፉ (የቀሩትም ኹሉ)።

ብርሃን ማያ ነው አይደል?  በመስቀሉ ብርሃን ድኅነትን፤  በልደቱ ብርሃን ዕርቅን፥ ሰላምን (ፍቅር አንድነትን)፥ በጥምቀቱ ብርሃን የእውነተኛው ሕዳሴ፥ የዳግም ልደት መሠረት የኾነውን ሕፅበት፤ በትንሣኤው ብርሃን ደግሞ ሕይወትን እናያለን። እናያለንና፦

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችኍ አደረሰን!

Thursday, November 21, 2013

Ethiopia's Foreign Relations Then and Now!


The following is an invaluable piece of document in which we find an extremely riveting story. It is a story not just interesting and entertaining to read, like some kind of fiction. Rather, it is a story as strongly inspiring as it is really real! For precisely which reason, however, it is a kind of story that “developmental” historians and researchers of all sorts, who have put themselves to the service of the Zeitgeist, would not want us to hear about. In fact this kind of story does not sit well with those who have a “grand plan” of fragmenting a great nation. But I believe it indeed is ennobling for us Ethiopians to know about it, even when we have fallen, alas, on such awfully hard times!

Sunday, October 27, 2013

ትንሣኤ ግእዝ 4

"ትንሣኤ ግእዝ"፦ Ge'ez Conversation 

Below is a link to a short Ge'ez conversation recorded by ELAT (Endangered Languages Alliance Toronto)

በኒውዮርክ ለጥፋት የቀረቡ ቋንቋዎችን ለመታደግ ጥረት የሚያደርግ አንድ ድርጅት አለ። በቅርቡ የዚያ ተመሳሳይ እኅት ድርጅት በቶሮንቶ ተቋቁሞ ሥራውን ጀምሯል።

ታዲያ በኲንስ ዩኒቨርሲቲ የምታስተምረው የቶሮንቶው ድርጅት መሥራች እና መሪ ስለ ግእዝ ኹናቴ ለመረዳት ፈልጋ ቃለ መጠይቅ አቅርባልኝ ጥቂት ተወያይተናል። ቃለ መጠይቁ በቪዲዮ የተቀረጸ ሲኾን፤ የአርትዖቱ ሥራ ገና አላለቀም።

ነገር ግን ግእዝ ምን ምን እንደሚል ልየው በማለት በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ተገኝታ ካየች በዃላ፤ እስኪ አንዱ ከሌላው ጋር ሲነጋገርበትስ ምን እንደሚመስል አሳዩኝ አለችን። እናም ይኸንን ቀረጸች፦http://www.youtube.com/watch?v=BMNtOldl1go

Friday, October 4, 2013

በእንተ ሃይማኖተ ሐራ (ስለ ጨዋ ሃይማኖት)

የሃይማኖት እዳው ገብስ አይደለም። ምናልባት ለነ ራስ-ብቻ-ደኅኔ ለነ ለኾድ-ብቻ-ዐደሮች እንዲያ ሊመስላቸው ቢችልም ቅሉ፤ ውዱ ጤፍም እንኳ ዋጋ አይኾነውም። ወርቅም ብርም አይኾኑም። አልማዝም ዕንቍም እንዲኹ። ወገኖቼ፦ የሃይማኖት እዳው ደም ነው። ቢመርርም እቅጩ የኸው ነው። የሃይማኖት እዳው ደም ነው።

Thursday, August 8, 2013

ትንሣኤ ግእዝ 3

 “ትንሣኤ ግእዝ”፦ ሥሯጽ (በእንተ ርእስየ)
...የቀጠለ
ባለፈው “ድንዝዝ” እንዳልኍ ስጠቁማችኍ ሳታዝኑልኝ አትቀሩም። “ለምን” ብላችኹም ጠይቃችኍ ይኾናል። እውነቱን ልንገራችኍ? ለመደንዘዜ ዋናው ምክንያት፦ አገራችን የምትገኝበት፥ ቤተ ክሲያናችንም ያለችበት አሳዛኝ ኹናቴ ነው። ዝርዝሩን ላቆየው። ይኽም በመኾኑ አንዳንዴ ነፍስ ስዘራ እንኳ፤ በዚያው ነፍስ በዘራኹበት ጊዜ ስላለው ያገራችን እና የቤተ ክሲያናችን ጠቅላላ ኹናቴ እንጂ፤ ስብስብ ብየ በተለይ ስለግእዝ ብቻ ለማሰብ አልቻልኹም (በማርች 2012 መጨረሻ እና በቀጣዩ ወር ካደረግኹት አንድ ጥረት በስተቀር፦ ይኸውም "የግእዝ ንባብ በቀላል ዘዴ"ን አዘጋጅቼ፤ ለቶሮንቶ ነዋሪዎች ለማስተማር ያደረግኹት ሙከራ ነው)።