Monday, November 15, 2010

ምልማደ-ንባብ (የንባብ መልመጃ) -1

"ምልማደ-ንባብ (የንባብ መልመጃ) -1" የሚለውን የዚህን ልጥፍ (ፖስት) ርእስ ይኮርኩሙት (Click on the Title of this particular Post above) ፤ ሲኮረኩሙት PDF በሚባለው የሰነድ ቅጽ (ፎርማት) የተዘጋጀ ባለምልክት "መልእክተ-ዮሐንስ" ያገኛሉ። እሱን እማስሊያዎ (እኮምፒውተርዎ) ታች-አራግፈው (ዳውንለውደው) ከምንባቡ ሥር ያለውን መመሪያ በመከተል የግእዝን ንባብ ይለማመዱ። ያስቸገረዎ ነገር ካለ ባስተያየት መስጫው ሳጥን ይጠይቁን።

ምናልባት ታች አልራገፍ ቢልዎ (in case you are not able to download it) እዚያው ባለበት ከግርጌ ያለውን ማጕሊያ በመጠቀም በደንብ እንዲነበብዎ ያድርጉና ይመልከቱት።

ንባበ-ግእዝ (የግእዝ ንባብ)

በግእዝ የተለያዩ ንባባት አሉ። እነዚህን ለይቶ ለማወቅ እና ጥሩ አንባቢ ለመኾን ወሳኙ መንገድ ከመምህራኑ እግር ሥር ቊጭ ብሎ ደረጃ በደረጃ በድምፅ መማር ነው። ነገር ግን በድምፅ ለመማር ዕድሉ ለሌለው በጽሑፍ ምልክቶችን በመጠቀም ማለማመድ ይቻል እንደኾነ ለመሞከር ያኽል የተዘጋጁ ጥቂት መልመጃዎችን እናቀርባለን። በቅድሚያ ግን ንባባቱን በምሳሌ ጭምር እንወቃቸው።

ንባብ፦
 1. ተነሽ = ባብዛኛው የቃሉን ቅድመ-መድረሻ ቀለም ይዞ ተኵሶ (እንደ ቁጣ ቢጤ) ማንበብ ነው
 2. ወዳቂ = የቃሉን መድረሻ ቀለም ይዞ አልዝዞ (እንደማላዘን ቢጤ) ማንበብ ነው
 3. ተጣይ = ኹሉንም ቀለማት እኩል ማንበብ ነው
 4. ተናባቢ = ኹለት ወይም ከዚያ በላይ ቃላትን እንዳንድ ቃል ባንድ ትንፋሽ ማንበብ ነው
 5. ሰያፍ = እንደተነሽ ነው ("ቅድመ-መድረሻ" የሚለው ቀርቶ)
 6. ማጥበቅ = ቀለሙን አጥብቆ ማንበብ
 7. ማላላት = አላልቶ ማንበብ
 8. አጎበር = ተነሽ፣ ሰያፍ፣ ተጣይ ንባባትን እንደ ሂ፣ ኒ፣ ሰ፣ ኬ ፣ አ ያሉ ሲከተሏቸው አጎበር ይባላል
ምሳሌ፦
 1. ተነሽ፦ ረ፣ ቀለ፣ ባከ፣ አእረ፣
 2. ወዳቂ፦ ፣ ቀዲ፣ ብእ፣ ደብተ፣ ጽ፣ ከበ
 3. ተጣይ፦ ማርያም፣ ትምህርት፣ መምህር፣
 4. ሰያፍ፦ ገብኤል፣ ኢሳያስ፣ ጳሎስ፣ ጥሮስ
 5. ተናባቢ፦ ቤተ-ክርስቲያን፣ ሥርዐተ-ቤተ-ክርስቲያን፣ ዕበየ-ክብረ-ስብሐት
 6. የሚጠብቅ፦ ሰሐ (ፍቺው "አመሰገነ" ሲኾን "ብ" ይጠብቃል፤ ይነሣማል)
 7. የሚላላ፦ ብሐ (ፍችው "ሠባ፣ ወፈረ" ሲኾን ደግሞ "ብ" ይላላል፤ ""ይነሣል)
 8. አጎበር፦ አነ፣ አብርሃም (እንደ ወዳቂ)፤ ቀዲሰ፣ ይእሰ (እንደ ተነሽ)
እነዚህን ንባባት ጠንቅቆ ማወቅ ማናቸውንም በግእዝ የተደረሱ ጽሑፎች በትክክል ለመረዳት አስፈላጊ ከመኾኑ ጋር፤ በቅኔ ቤት እና በዜማ ቤት እንዲኹም በትርጓሜ መጻሕፍት ጉባኤ ለሚቀጥለውም ትምርት መሠረት ነው። ስለኾነም "ሀ" ተብሎ በ"ቊጥር" የሚጀመረውይህ መሠረታዊ የንባብ ትምህርት እስከ"ድጋም" የሚደርሰው የሚከተሉትን ሦስት ደረጃዎች አልፎ ነው፦
 1. ግእዝ
 2. ወርድ
 3. ዐቢይ (ቊም)
ስለንባብ ስልቶች ሊቁ ደስታ ተክለ-ወልድ በምሳሌ አጣጥመው የገለጹትን "ዋዜማ" በሚባለው ገጽ መመልከት ይቻላል፦

http://gzamargna.net/html/fidelawariya.html

የሊህንም ጣዕም ለማቅመስ ያኽል የድምፅ ቅጂ አዘጋጅተን እዚሁ አያ
ዘን ለማቅረብ እንሞክራለን።

Thursday, November 11, 2010

ፈቲነ-ብርዕ (የብርዕ ሙከራ)

 • አ ግእዝ/አንደኛ/first order
 • ኡ ካዕብ/ኹለተኛ/second order
 • ኢ ሣልስ/ሦስተኛ/third order
 • ኣ ራብዕ/ዐራተኛ/fourth order
 • ምስ/ዐምስተኛ/fifth order
 • እ ሳድስ/ስድስተኛ/sixth order
 • ኦ ሳብዕ/ሰባተኛ/seventh order
'አ' እንደ '' ሳይኾን እንደ '' ቢነበብ እንዴት ጥሩ ነበር። ለማንኛውም ከ'አ፣ ዐ' እና ከ 'ሀ፣ ሐ፣ ' በቀር በሌሎቹ ፊደላት ኹሉ የ'ግእዙ' ድምፅ '' መኾኑ ይታወቃል፤ እነ'አ' እና 'ሀ'ም ቢኾኑ ጥንቱን ከሌሎቹ ፊደላት በተመሳሳይ ኹናቴ የሚነበቡ እንጂ 'ግእዛቸው' ከ'ራብዓቸው' አይዛነቅ እንደነበረ አንዳንድ ማስረጃዎች አሉ። ስለዚህ ስለአንዱም አንዱ ፊደል "ግእዝ/አንደኛ/first order" በምንልበት ጊዜ ያ ፊደል ከ'' ጋራ ሲዋሐድ የሚያሰማውን ድመፅ ለማመልከት ነው። ከዚሁም ጋር "ግእዝ" ማለት "አንደኛ" ማለትን የሚያሰማ መኾኑን ልብ በሉ።

  ፈቲነ-ሰሌዳ (የሰሌዳ ሙከራ)፦ በስመ እግዚአብሔር ሕያው ዘይሰመይ አልፋ፤ ወሀቤ ፊደል ተስፋ፤ ወጸጋዌ መምህር ሱታፋ...