Sunday, December 5, 2010

ምልማደ-ንባብ (የንባብ መልመጃ) -2

አኹንም "ምልማደ-ንባብ (የንባብ መልመጃ) -2" የሚለውን የዚህኛውን ልጥፍ (ፖስት) ርእስ ይኮርኵሙና የሚከፈትልዎን ከዘወትር ጸሎት የተወሰደ ባለምልክት ንባብ መላልሰው ይለማመዱ።

መልመጃው በጥንተ-ተፈጥሮው በተለይ ለጃማይካውያን ታልሞ የተዘጋጀ ስለነበረ፤ አነባበቡን በሮማይስጥ ፊደልም ጭምር ለማሳየት ተሞክሯል። ይኸም ከሚጠቅም በቀር የሚጎዳው ነገር እንደሌለ ስለገመትን ገንጥሎ ማስቀረት አያስፈልግም በሚል እንዳለ አያይዘን አቅርበነዋል።

2 comments:

 1. ባካችኹ፣ ባካችኹ አንድ በግእዝ ንባብ እጅግ በጣም የተለመደ ስሕተት አስወግዱ:- ቅጽል ከባለቤት ማናበብ።

  ቅጽል ከባለቤት አይናበብም!

  ምሳሌ፦ "...አሐዱ አምላክ" በሚለው ሐረግ "አሐዱ" የ"አምላክ" ቅጽል እንጂ፤ "አምላክ" የ"አሐዱ" ዘርፍ አይደለም።

  ስለዚህ "አሐዱ"ን ከ"አምላክ" በደንብ ለይታችኹ አንብቡ። በዚያውም ላይ "አሐዱ" ወዳቂ መኾኑን አትዘንጉ።

  ይህን ለማለት የተገደድኹት፤ ይህንን ሐረግ እንደተናባቢ ቀለም "አሐዱ-አምላክ" ብለው ባንድ ላይ ሸምጥጠው የሚያነቡ ቁጥራቸው ተቢሊዮን ዝቅ ቢልም ተሚሊዮን ግን አጅግ ከፍ ስለሚል ነው። "የተማሩ" እንደኾኑ ከሚያስቡትም ሳይቀር። ያልተማሩ እናቶቻችን አነባበብ'ማ ቢጣፍጥ እንጂ አይደንቅም "በስመ-አብ"ን እንኳ "በስማም" አይደል የሚሉ!

  ReplyDelete