Saturday, March 10, 2012

ድንጋጌ (Definition)

ሙባእ (መግቢያ)

ያንድን ነገር ባሕርይ/ምን-()ነት (essence) መናገር ቀላል አይደለም፤ በተለይ የፅንሰ-ሓሳቦች ድልድል ከታኦርያው (ከቲዎሪው) መደብ አልፎ በተግባራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያስከትለውን ተጽእኖ ለሚያስተውል።
ከኦሪት ዘፍጥረት የመጀመሪያ ምዕራፍ እንዲሁም በጽርኣውያኑ አብነት ከናፍላጦን እና አርስጣጣለስ ከነርሱም በፊት ከነበሩ ፈላስሞች ጊዜ ጀምሮ--(እንዲያውም ትክክለኛ መነሻውን ለማግኘት ጠበቅ አድርገን ወደ እንግፋውና፤ ከኢትዮጵያዊው ቶት-ሄርሜስ ዘመን ጀምሮ)--እስካሁን ድረስ በዘለቀው፤ ፍጥረታለምን (ፍጥረተ-ዓለምን/ፍጥረታትን/ህላዌያትን/ህልዋንን/ማናቸውንም ነዋሪ ነገሮች) በየወገናቸው ለይቶ ለማስቀመጥ በሚጥረውየጸዋትወ-ነገር (የምስትውዳያት) ታኦርያ” (theory of categories) እንዲሁም የፍጥረታትን ባሕርይ/ምን-()ነት፣ ለመወሰንም ኾነ አናዎራቸውን (ህላዌያቸውን) ለመረዳት በሚጥረውንባበ-ህላዌ” (ontology) በሚባለው የፍልስፍና ክፍል የሚወጣ የሚወርደውን ዐተታ ላንድ አፍታ የተመለከተ ብልህ ተማሪ፦አንዱም-አንዱ ዕሳቤ (ፅንሰ-ሓሳብ) ከቀዋሚ ባሕርይ ይልቅ ኺደታዊ ጠባይ ጎልቶ እንደሚታይበት ይገነዘባል። ስለኾነም እንዲህ ያለው ጥረት መጨረሻ አይገኝለትም ብሎ ባይደመድምም ስንኳ፤ ድርሱ እጅግ ሩቅ እና ጥልቅ መኾኑን ግን በመጠኑ መረዳት አይሳነውም። 
  
ይኹን እንጂ በኾነው ምክንያት እንነጋገር ዘንድ ስንሻ፤ እንዲያው ተደበላልቆ፣ ተዛንቆ፣ ተዘበራርቆ ከሚገኘው ውጥን-ቅጥ፤ በዓይነሥጋም ይኹን በዓይነልቡና አንዱንም-አንዷን ነገር ነጥለን ለማየት እና ለማሳየት፦ ወይ ራስ ቆርቶ አለያም ስም ጠርቶ በመጠቆም ነገርዮውን (ወደነገርዮው) “ማመ᎐ር፣[1] ማመልከት አይቀሬ ነው። እንዲህ ለመነሻ ያኽል በቀላሉ ጠቁመን ወይ ጠቅሰን የምናንጠለጥለውንም አንዳች ቅንጣት፤ እንዲያው በድፍኑ ከወዲያ ወዲህ እያንከባለሉ እና እያድበለበሉ ለመጫወት ሳይኾን፤ ምን-እነቱን በምር ተረድቶ እና አስረድቶ ከልብ ለማስገባት እና እዚያም አደላድሎ ለማስቀመጥ ብቻ ሳይኾን፤ የተዘምዶ ተግባሩን እንዲፈጽም ለማስቻል ግን፤ የተለያዩ ገጽታዎቹን፣ ገንዘቦቹን፣ ወዘተ. ጠቅልለው የያዙትን ዕሳቤዎች/ፅንሰ-ሐሳቦች (con-cepts) በከፍተኛ ጥንቃቄ እየሰለቱ፣ እየበለቱ መደንገግ እና ማብራራት ግድ ይኾናል። በተለይ ግሡሣን ስላይደሉ ረቂቅ ነገሮች እንዲያው በቃላት ብቻ የቋጠርነው ዕሳቤ/ፅንሰሐሳብ (con-cept) የሚያመለክተው ነገር ለራሳችን በጥልቅ እንዲገባን እና የቃሉ ቃላዊ ትርጉም ብቻ ሳይኾን በቃሉ አማካይነት የጠቆምነው ክስተት ወይም ነገርዮ (thing/phenomen/being/entity/trope) ጭምር ለሌሎች በዓይነ-ልቡናቸው ወለል ብሎ እንዲታያቸው የፅንሰሐሳቡን ቋጠሮ በሚገባ ማፍታታት ያስፈልጋል። ይህም የፍልስፍና ዐይነተኛ ሥራ ነው። 

እንዲህ የኾነ እንደኾነ፤ ካንዱም አንዱ ዕሳቤ ጋራ ትይይዝ ባላቸው ተግባራዊ ጉዳዮች ላይ በሚደረጉ ውይይቶች--ብሎልን ብንስማማ፣ ሳይልልን ብንጣላም--ቢያንስ ቢያንስ ባካኼዳችን አራምባ እና ቆቦ እየዘለልን ባዶ ቃላትን በማንኳኳት ከመደናቆር፤ አንድ ዐይነት ጕዳይ-ዐዘል መነሻና መድረሻ ወስነን ለመከራከር እንችላለን። ስለዚህ ቋንቋ-ነክ በኾኑ ዕሳቤዎች የተቋጠሩ ዐይነተኛ ነገሮችን ለመረዳት ፅንሰሐሳቦቹ የተቋጠሩባቸውን ቃላት በመጠኑ በማፍታት ለመመልከት እንሞክራለን።[1] በግእዝአመብሎ ባማርኛአመለከተይላል።አመረብሎ (“ አላልቶ አንብቦ) ወይም በተለምዶአእመረብሎዐወቀይላል። ማመልከትና ማወቅ አንዳች ትይይዝ ይኖራቸው ይኾን?

3 comments:

 1. ባሀከ ኦ አቨውየ አንሰ ከበርኩ አንሶሱ ከመ እገኒ ለከ ፡ አይቴ ሀሎከ ኦ አበውየ መምክር ምህረኒ ልሳነ ግእዝ ወፈኑ ሊተ በፃህፍተ ወድርሳት ከመይፈትሁ ልሳንይ፡፡እስመ አልብየ ዝየ አይትነበብ ......  ማህበረ ቅዱሳን የተባለ ህገወጥ ፓርቲ ህገወጥነቱንና ዘረኝነቱን ያረጋገጠው በጣም የገረመኝ በስላሴ ቤተክርስትያን የሚገኘው የደርጉ ጳጳስ ሀውልት ቅርስ ብሎ ሲያስጠግነው ያቡነ ጳውሎስ ደግሞ ጣኦት እያለ ሲሰብክበት በገዛ ራሱ በፃፈው አንብቤ ነው፡፡ አረ ይከ ፓርቲ በተስክያናችን ማተራመሱን ትቶ ካርድ ይዞ ምርጫ ቢቀሰቅስ ይሻለዋል፡፡ ለነገሩ በዴሞክራሲ መቸ ያምናል? ምንድን ነው እየሰራ ያለው?ቤተክርስትያን ለፀሎት የመጣውን ምእመን በጠበጠው እኮ አበው በቃ ዝም ትላላቹ?
  ሁለቱም የጀሶ ሀውልቶች ጣኦት ከሆኑ አንድ ላይ ቅርስ ከሆኑ አንድ ላይ እንጂ በየተኛው አስተሳሰብ ነው የ 1ዱ ጣኦት ሆኖ የሌላው ቅርስ የሚሆነው? ይክ በዘረኝነት አስተሳሰብ ብቻ ነው፡፡ ማህበሩ እንደ መረጃ ያቀረበው በደርግ የነበሩ ሊቀጳጳስ በባዶ እግራቸው መሄዳቸሀውን ነው! በሁለተኛነትም ብር አለመቅጠራቸውን ነው! ይሁን እንጂ የዛኔ ዘመን ጥሩ በነበረበት ይሰበሰብ የነበረውን መባ የት ያደርጉት ነበር ?ተብሎ ቢጠየቅ መልሳቸው እዜር ይወቅ፡፡ በደርግ መውጫ ሰአት ክርስትያን የእስላም ስጋ ሊበላ በታወጀበት ብፁአን ጳጳሳት ሲሰዉም አገር ሲለቁም ተመቻችተው ተኝተው የነበሩ ጳጳስ ብፁእ መባላቸው ከፖለቲካ ውጪ ሌላ ምክንያት የነውም፡፡
  ደግሞም እኔ በባዶ እግር መሄዴ ብፁእ ሊያስብለኝ የሚችል ሀይማኖታዊ ይዘት የለውም፡፡እመቤታችን እንክዋን ? "ወአስተየቶ ለፅሙእ ከልብ በአሳእኒሀ " ይባል የለም እንዴ ስለዚ በናንተ ዘረኛ አስተሳሰብ የደሩጉ ጳጳስ ከእመቤታችን ይበልጣሉ ማለት ነው? ወይስ ምን መረጃ ይዛችሁ ነው የምትዘባርቁት?

  ReplyDelete
 2. ባሀከ ኦ አቨውየ አንሰ ነበርኩ አንሶሱ ከመ እገኒ ለከ ፡ አይቴ ሀሎከ ኦ አበውየ መምክር ምህረኒ ልሳነ ግእዝ ወፈኑ ሊተ በፃህፍተ ወድርሳት ከመይፈትሁ ልሳንይ፡፡እስመ አልብየ ዝየ አይትነበብ

  ReplyDelete