Friday, December 28, 2012

ደቂቀ እምየ ተበአሱ በእንቲአየ

“ደቂቀ እምየ ተበአሱ በእንቲአየ”

ተራኮትን' እናንተው። እስ በሳችን። ስለእናታችን ልጅ። ነገሩ እንዲያ በኾነ ባልከፋ። መራኮታችን፦ ርስ በርስ፣ ምክንያቱም፦ ለናታችን ልጅ ስንል ከኾነ፤ መስማማታችን አይቀርም። መስማማታችን አይቀርምና፥ መስማማታችን ካልቀረ ዘንድ መራኮታችን "ከፍቶ አይከፋም" ያሰኛል።

ነገር ግን (አኹን ግዙፍ ግን መጣ) ነገር ግን መራኮታችን ወገን ተባዕድ ለይተን፤ ምክንያቱም ስለናታችን ልጅ ሳይኾን ስለሌላ ጥቅም ከኾነ፤ ያኔ የናታችንን ልጅ ይዘን መውጫ የሌለው ጥልቅ ሸለቆ ውስጥ መግባታችን ነው።

እስኪ ያለንበትን ኹናቴ በግሥ እናትተው።

ማለትም በማሕልየ መሐልይ ዘሰሎሞን የሰማነውን የቤተ እስራኤልን ድምፅ ለቤተ ተዋሕዶ ዘኢትዮጵያ እንግሠሥላትና [1] ምን እንደምትለን እንስማ፦

[1] የቀድሞ ታሪክ ወይም ድርሰት ለወቅታዊ ርእሰ ጉዳይ መግለጫነት ሲውል በቅኔ ቤት “ግሥ መንገድ” በዜማ “ግሥ መግሠሥ” እንዲሁም በትርጓሜ “በግሥ መናገር” ይባላል። 

Thursday, December 20, 2012

ፍትሐ ነገሥት እንዲህ ይላል፦

ወለሰብአ ኅርየት ይደልዎሙ ከመ የሀብዋ ለዛቲ ሢመት ለዘድልው ላቲ።
መራጮች ይህችን ሹመት ለሚገባው ሰው ሊሰጧት ይገባቸዋል።
ወእመሰ አበዩ ይከውኖሙ አበሳ።
የሚገባውን ትተው የማይገባውን ቢሾሙ እዳ ይኾንባቸዋል። ምቀኝነት ነውና።
ወኢይደሉ ከመ ትኩን ዛቲ ሢመት ለ፪ በ፩ ዘመን ወበ መንበር።
ባንድ ዘመን ባንድ ወንበር ኹለት ሰዎች ሊሾሙ አይገባም።... 'ባንድ ወንበር ኹለት መምር' እንዲሉ።
ወእመሰ ኮነ በአሐዱ ሀገር ትጽናዕ ለዘተሠይመ ቅድመ።
ባንድ ሀገር ኹለት ሰዎች ተሹመው ቢገኙ አስቀድሞ ለተሾመው ሰው ትጽናለት።

ፍትሕ መንፈሳዊ (አንቀጽ 4 ቍጥር 67 እና 68)
Period!!!


Wednesday, October 10, 2012

Come On Ethiopia: Come Home!


The word Ethiopia names a country. It also names a people, the great people of the country called Ethiopia.

Tuesday, July 10, 2012

Of the Old Suspicion and the New Vacuum


Of the Old Suspicion and the New Vacuum: Ethiopia’s Elite Then and Now

Suspicion is one of the main traits of which foreign diplomats and intellectuals used to accuse Ethiopia’s elite of the old times—scholars and warriors alike—

Thursday, April 5, 2012

ሆሲአ-ና፣ አድኅንሶ፣ አድነነ፦ አኹን፣ አኹን፣


“ሆሳዕና” የሚለው ጽራሕ/ጸሎት (ጩኸት/ጸሎት) ሥርወ-ቃሉ ዕብራይስጥ ሲኾን አቻ የሚኾነው ባሕርያዊ የግእዝ ቃል “አድነነአ”፣ “አድኅንሶ” ነው።
ይኸውም “አድን! አኹን አድን! አቤቱ አድን! አድና! አድነነ!” ማለት ነው። በመዝሙረ-ዳዊት 117 (118)፡25 አና ያህዌህ ሆሺዓ-ና!" = “ኦ እግዚኦ አድኅንሶ” (አቤቱ አድነና! አድነን አቤቱ! አድነነ! = Ah now, O LORD, save me/us!) ይላል። ይኽንን ጥቅስ ባንድ ያማርኛ አብነት “አቤቱ ባክኽ አኹን አድን” ብለው ፈተውት አንብቤኣለኹ። ማለፊያ ነው። ትክክለኛ ስሜቱ የሚገኘው ግን ሊቃውንት ሲናገሩት በመስማት ነው። በቃል ብቻ ሳይኾን ባቀዋወል፣ በነገር ብቻ ሳይኾን ባነጋገር፣ በንባብ ብቻ ሳይኾን ባነባበብ ልዩ የትርጕም ስሜት እንደሚተላለፍ፤ ጉባኤ ቤት የዋለ ያውቀዋል። 

ዃላ ግን “ሆሳእና” መሠረቱን ሳይለቅ እንደረቂቅ ስም ተወስዶ “መድኀኒትነት፣ መድኀኒት መኾን፣ መድኀኒት መባል፥ መድኀኒት” ተብሎ ተፍትቷል። በወንጌል “ሆሳዕና ለወልደ-ዳዊት” ሲል “ለዳዊት ልጅ ለክርስቶስ፦ መድኀኒትነት፣ መድኀኒት መኾን፣ መድኀኒት መባል ይገባል።” ማለቱ ነው። "ሆሳዕና በአርያም" ማለትም "በአርያም/በሰማይ ያለ መድኒት" ማለት ነው።

ከዚህም በቀር ለበዓሉ ዕለት ቅሉ ስም ኾኗል። ለምሳሌ በዶሮዎች ዘፈን ሆሳዕና የሚወክለው የበዓሉን ዕለት ነው፦ “በሆሳዕና ተሰበሰብና፤ በሳምንቱ አለብነ ሞቱ!” (ዶሮች ሲዘፍኑ ደግሞ የት አያችዃቸው የሚለን ቢኖር መልሳችን፦ "ዘሰ አጥረየ ዳፈ የአምር ምሳሌ" (መምህርን ገንዘብ ያደረገ ሰው ምሳሌ መስለው የነገሩትን ያውቃል) የሚለው የጠቢቡ ቃል ነው።)

ከዕለቱም ዐልፎ በሆሳዕና ለሚያዘው ሰሌን፣ የሰሌን ቅጠል፣ ቈጽለ-ዘይት፣ ባርሰነት፣ ኲሓ ለመሰለው ኹሉ መጠሪያ ኾኗል።

ወደመሠረታዊ ትርጕሙ እንመለስና፦

እስኪ ባካችኹ እኛም ዛሬ በምር “አቤቱ አድና!” እንበለው፤ እሱም ከምር ያድነና! ረ ያድነን! ያድነን እንጂ!

መቼ?

አኹን ነዋ። አኹን! አኹን!...

በዓሉን በዓለ ፍሥሓ ወሰላም ያድርግልን!


Monday, March 12, 2012

ንዒ ንዒ ንባበ-ግእዝ...


እንበልና፦

አንድ ልጅ ቅኔ ተምሮ የታወቀ ሊቅ ለመኾን ፈልጓል።

Saturday, March 10, 2012

ቋንቋ


እውን "ቋንቋ እንደ ዶማና ዲጂኖ የመጠቀሚያ መሳሪያ እንጂ ሌላ ምንም ማለት አይደለም"[1]? ቋንቋ እንዲያ ከኾነ ሰውስ ቢኾን ከመሣሪያነት ዐልፎ ሠሪ ሊኾን የሚችለው እንዴት ነው? ወይስ፦ ሰውም እንደ ዶማና ዲጂኖ ያው መሣሪያ ነው?


ድንጋጌ (Definition)

ሙባእ (መግቢያ)

ያንድን ነገር ባሕርይ/ምን-()ነት (essence) መናገር ቀላል አይደለም፤ በተለይ የፅንሰ-ሓሳቦች ድልድል ከታኦርያው (ከቲዎሪው) መደብ አልፎ በተግባራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያስከትለውን ተጽእኖ ለሚያስተውል።

Friday, March 9, 2012

ስለኹለቱ ሥርዐታተ-ተምህርት

መወድስ

(ፍሬ መወድስ፦ “ፍታሕ ሊተ እግዚኦ ወተበቀ፟ል በቀልየ!”)

በውስተ᎘ ቤታ ለእም ኢትዮጵያ
ጉቡኣነ ደርገ እንዘ᎘ ይዛውዑ ዛውዐ
ከንቶ ነገረ እለተናሥኡ ኵርናዐ
ጠባይዐ᎘ ቀደምት ኣሐደ[1] ወትምህርተ᎘ ደኀርት ካልዐ
መኑመ፟ እንበለ᎘ ዘሀሎ ያስተሳልም ስምዐ
ለለአሐዱ እምዘአምዕዐ፤
ብሂለ᎘ ጠዋይ ጠዋየ ወብሂለ᎘ ርቱዕ ርቱዐ

(ለዓለም፦ “ለዓለም ወለዓለመ᎘ ዓለም!”)

መምህረ᎘ ሕግሂ ድኅርና ግዕዘ᎘ ካልዑ ዘጠግዐ
ቅድምና ባሕርየ᎘ ርእሱ ፍጹመ በዘአጽንዐ
እምውሉደ᎘ ምዕራብ አብያጺሁ እለልማዶሙ ፀዕዐ
ላሕየ᎘ ጉባኤሁ ይሤኒ ዳዊት ከመአይድዐ

ትርጕም

Tuesday, February 14, 2012

ኢትዮጵያ ለግብጽ፦ ልጅ ስትኾን እናት!


ጉባኤ-ቃና

እመ-ኢያእመርኪ ግብጽ ቄርሎስሃ ርእሰኪ ፍጹመ
ኢትዮጵያ ትኩንኪ እንዘ-ወለትኪ እመ

ትርጕም

ግብጽ ሆይ! ፍጹም የኾነ ራስሽ ቄርሎስን ካላወቅሽ
ኢትዮጵያ ልጅሽ ስትኾን እናትን ትኹንሽ። 


Copt/Egypt! if thou know not Cyril, thyself, full of wonder,

Let Ethiopia be your mother, while daughter.

Wednesday, February 8, 2012

የመልአከ-ብረሃን አድማሱ ጀንበሬ መወድስ (ስለ ኤኩሜኒዝም)


[ባለፈው ክታባችን የጠቀስነው ቅኔ ትርጕም]

አባ አየለ የተባለ ካቶሊካዊ መነኵሴ፤ (በራሱ ምርምር አግኝቶት ሳይኾን ኢግናሲዮ ጕዪዲ የተባለ ጣሊያናዊ አዘጋጅቶ ያስቀመጠውን ገልብጦ) ለዶክትሬት ማዕርግ በበቃበት ጽሑፉ፤ ኢትዮጵያ ሃይማኖቷን ባታውቀው ነው እንጂ፤ ስለክርስቶስ “አካላዊ” ተዋሕዶ የምታምነው ነገር’ኮ ከሮማ ቤተ ክርስቲያን ትምርት አይለይም፤ ውስጡ ሲፈለፈል ያው “ኹለት ባሕርይ” የሚል ነው ለማለት ደፍሮ ነበር። ይኽንኑ ጽሑፉን በሮማ ካርዲናሎች መቅድም አሳጅቦ በጣሊያንኛ አዘጋጅቶ ባቀረበ ጊዜ፤ አቦ-አቦ እንጂ ሐይ የሚለው ባለማግኘቱ፤ ጥሩ ነገር የሠራ መስሎት ወዳማርኛ መልሶ ሊያሳትመው ችሏል። ደግነቱ ጊዜው ሊቃውንት ያልጠፉበት ዘመን ስለነበረ፤ አባ አየለ መጽሐፉን ከማን እንደቀዳው በሚገባ ባይደርሱበትም፤ የነገሩን ፍጹም ሐሰትነት ግን ከያቅጣጫው የተነሡ ሊቃውንት አስረድተዋል። ከነርሱም መካከል መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ያባ አየለን “ተነ-ሐሳብ” (የዐሳብ ብናኝ) በትንትኑን አውጥተው ድራሹን ባጠፉበት “መድሎተ-አሚን” (= የሃይማኖት ሚዛን) በተሰኘ መጽሐፋቸው ገጽ 242 እና 243 ላይ የሚከተለውን አስፍረውልናል፦

Thursday, February 2, 2012

ግእዝ እና ንባበ-መለኮት፦ ለእስ-በስ ውይይት (Geez and Theology: A Colloquy)[ይችን የምክታብ ድረ-ገጽ (“ግእዝ በመሥመር ላይ”ን) ከሠየምናት ዓመት ኾነን። ሥራውን እንዳጀማመራችን ሳንቀጥል እንደገና ወደዃላ ተመልሰን እስካኹን በዝግጅት እየባተልን አለን። ይኹን እንጂ የግእዝ መፍቀርያን የቱን ያኽል እንደኾኑ፤ ፌስቡክ በተባለው የገጽ መጣፍ ላይ ባለን አድራሻ በነጻ መወዳጀት የሚቻለውን የጓደኞች ቊጥር (5000) ገና ዓመት ሳይሞላን ገደቡን ማለፋችን አስደምሞናል። እሶ፣ እሰይ፣ ግእዝ አኹንም ዘመደ-ብዙ ነው ለካ! እንዲህ ነውና እኛም ትምርቱን አጠናክረን እንቀጥላለን። ዛሬ ግን፤ ከቋንቋው ጋር ትይይዝ ባለው አንድ ሃይማኖታዊ ጕዳይ ላይ እንተኩራለን።]