Thursday, January 10, 2013

ግፍ ገዘፈ!

በብዙ መንገድ እንደምናየው፦ ግፍ ገዘፈ! ግፍ ሲገዝፍ በግእዝ "ህላዌ ግፍዕ" ይባላል። የኛ ህላዌ፥ የኛ ኑሮ እንዲያ ኹኖ መቅረቱ ነውን--ግዙፍ ግፍ? ይኹን እንጂ፥ ይኹንና ፦ ለኛ ግን ያባታችን የሄኖክን ቃል መስማት ይሻለናል። 
ወእነግረክሙ ፍቁራን፦ አፍቅርዋ ለርትዕ ወባቲ ሑሩ። ወኢትቅረቡ ኀበ ርትዕ በክልኤ ልብ ወኢትኅበሩ ምስለ እለ በክልኤ ልብ። አላ ሑሩ በጽድቅ ደቂቅየ። ወይእቲ ትመርሐክሙ በፍናዋት ኄራት። ወጽድቅ ይከውን ለክሙ ሱታፌ። እስመ አአምር ከመ ይጸንዕ ህላዌ ግፍዕ ወትትፌጸም መቅሠፍት ዐቢይ ዲበ ምድር። ወትትፌጸም ኩላ ዐመፃ ወትትገዘም እምሥረዊሃ። ወኩሉ ሕንፃ የኀልፍ...
ወዳጆቼ እነግራችዃለኊ፦ፍትሕ-ርትዕን/ሕግን ውደዷት በሷም ኺዱ። ኹለት ልብ ኹናችኊ ወደሕግ አትቅረቡ፤ ኹለት ልብ ከኾኑም ጋራ አትተባበሩ። በጽድቅ/በእውነት ኺዱ እንጂ፤ ልጆቼ። ርሷም በቀና መንገድ ትመራችዃለች።  ጽድቅም ድጋፍ ይኾናችዃል። የግፍ ሥራ እንዲገዝፍ፥ እንዲጸና፤ በመጽናቱም በምድር ላይ ታላቅ መቅሠፍት እንዲፈጸም አውቃለኊና። ዐመፃ ኹላ ከሥሯ ተቆርጣ ትጠፋለች። ሕንፃም ኹሉ ያልፋል... 
ዘተወክፈ ነቢየ በስመ ነቢይ ዐስበ ነቢይ ወእሴተ ነቢይ ይነሥእ ወይረክብ እምኀበ እግዚአብሔር አምላኩ!
ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢዩን ዋጋ የነቢዩን በረከት ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል!

No comments:

Post a Comment