Thursday, November 21, 2013

Ethiopia's Foreign Relations Then and Now!


The following is an invaluable piece of document in which we find an extremely riveting story. It is a story not just interesting and entertaining to read, like some kind of fiction. Rather, it is a story as strongly inspiring as it is really real! For precisely which reason, however, it is a kind of story that “developmental” historians and researchers of all sorts, who have put themselves to the service of the Zeitgeist, would not want us to hear about. In fact this kind of story does not sit well with those who have a “grand plan” of fragmenting a great nation. But I believe it indeed is ennobling for us Ethiopians to know about it, even when we have fallen, alas, on such awfully hard times!

Sunday, October 27, 2013

ትንሣኤ ግእዝ 4

"ትንሣኤ ግእዝ"፦ Ge'ez Conversation 

Below is a link to a short Ge'ez conversation recorded by ELAT (Endangered Languages Alliance Toronto)

በኒውዮርክ ለጥፋት የቀረቡ ቋንቋዎችን ለመታደግ ጥረት የሚያደርግ አንድ ድርጅት አለ። በቅርቡ የዚያ ተመሳሳይ እኅት ድርጅት በቶሮንቶ ተቋቁሞ ሥራውን ጀምሯል።

ታዲያ በኲንስ ዩኒቨርሲቲ የምታስተምረው የቶሮንቶው ድርጅት መሥራች እና መሪ ስለ ግእዝ ኹናቴ ለመረዳት ፈልጋ ቃለ መጠይቅ አቅርባልኝ ጥቂት ተወያይተናል። ቃለ መጠይቁ በቪዲዮ የተቀረጸ ሲኾን፤ የአርትዖቱ ሥራ ገና አላለቀም።

ነገር ግን ግእዝ ምን ምን እንደሚል ልየው በማለት በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ተገኝታ ካየች በዃላ፤ እስኪ አንዱ ከሌላው ጋር ሲነጋገርበትስ ምን እንደሚመስል አሳዩኝ አለችን። እናም ይኸንን ቀረጸች፦http://www.youtube.com/watch?v=BMNtOldl1go

Friday, October 4, 2013

በእንተ ሃይማኖተ ሐራ (ስለ ጨዋ ሃይማኖት)

የሃይማኖት እዳው ገብስ አይደለም። ምናልባት ለነ ራስ-ብቻ-ደኅኔ ለነ ለኾድ-ብቻ-ዐደሮች እንዲያ ሊመስላቸው ቢችልም ቅሉ፤ ውዱ ጤፍም እንኳ ዋጋ አይኾነውም። ወርቅም ብርም አይኾኑም። አልማዝም ዕንቍም እንዲኹ። ወገኖቼ፦ የሃይማኖት እዳው ደም ነው። ቢመርርም እቅጩ የኸው ነው። የሃይማኖት እዳው ደም ነው።

Thursday, August 8, 2013

ትንሣኤ ግእዝ 3

 “ትንሣኤ ግእዝ”፦ ሥሯጽ (በእንተ ርእስየ)
...የቀጠለ
ባለፈው “ድንዝዝ” እንዳልኍ ስጠቁማችኍ ሳታዝኑልኝ አትቀሩም። “ለምን” ብላችኹም ጠይቃችኍ ይኾናል። እውነቱን ልንገራችኍ? ለመደንዘዜ ዋናው ምክንያት፦ አገራችን የምትገኝበት፥ ቤተ ክሲያናችንም ያለችበት አሳዛኝ ኹናቴ ነው። ዝርዝሩን ላቆየው። ይኽም በመኾኑ አንዳንዴ ነፍስ ስዘራ እንኳ፤ በዚያው ነፍስ በዘራኹበት ጊዜ ስላለው ያገራችን እና የቤተ ክሲያናችን ጠቅላላ ኹናቴ እንጂ፤ ስብስብ ብየ በተለይ ስለግእዝ ብቻ ለማሰብ አልቻልኹም (በማርች 2012 መጨረሻ እና በቀጣዩ ወር ካደረግኹት አንድ ጥረት በስተቀር፦ ይኸውም "የግእዝ ንባብ በቀላል ዘዴ"ን አዘጋጅቼ፤ ለቶሮንቶ ነዋሪዎች ለማስተማር ያደረግኹት ሙከራ ነው)። 


Wednesday, July 31, 2013

ትንሣኤ ግእዝ 2

...የቀጠለ 

 “ትንሣኤ ግእዝ”፦ በባዕድ አገር 


ኹለት ስሞች ልስጣችዅና ጎጕሏቸው (ታሪካቸውን በጕግል አማካይነት እየጎለጎላችኍ አውጡት ማለቴ ነው፤ እንድታነቡት)፦ ሂዮብ ሉዶልፍን እና ኦገስት ዲልማንን (Hiob Ludolf and August Dillmann)። እሊኽ የአለማኝ (የጀርመን) ምሁራን፤ በምዕራቡ ዓለም የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር መሥራች እና ዐዳሽ ተብለው ይታወቃሉ ፤ እንደስማቸው ተራ። ይኸውም ሉዶልፍ በዘመናዊው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያን ሃይማኖት፥ ታሪክ እና ባህል፥ ቋንቋዋን ግእዝንም በስፋት በማስተዋወቅ፤ ኢትዮጵያ በተለያዩ ያውሮፓ የትምርት ማእከላት በምር እንድትጠና ያስቻለ ሲኾን፤ በጊዜ ብዛት ጥናቱ እየቀዘቀዘ ሲመጣ፤ ዃላ ዲልማን ተንሥቶ ምርምሩ እንደገና እንደዐዲስ እንዲያብብ አድርጎታልና ነው። 
ሂዮብ ሉዶልፍ

Friday, July 26, 2013

ትንሣኤ ግእዝ


ግእዝ፦ የሞተ ወይስ ለጥፋት የቀረበ ቋንቋ?
(Is Geez a dead language or an endangered one?)

የመርበብቱ ዓለም ራሱን የቻለ መኖሪያ ቦታ ነው ባይባልም፤ ብዙ ዓይነት ማኅበረሰቦች ብዙ ዓይነት ጕዳይ የሚጐድዩበት ልዩ ልዩ ተግባር የሚያከናውኑበት የማይናቅ ክፍለ ዓለም መኾኑ ግን የሚያጠራጥር አይመስለኝም። በበኩሌ ይኽንኑ ዐዲስ እውነታ በፈረንጆቹ 2002 ገደማ በምር ስለተገነዘብኍ፤ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ትምርት እና ሥራት በዚኹ ክፍለ ዓለም (ማለትም፦ በመርበብቱ ዓለም፤ i.e., on the internet) በስፋት እንዲወከል ፍላጎት ተቀሰቀሰብኝ። እናም ወዲያውኑ “ሊቅነት በኢትዮጵያ” ምን ይመስል እንደነበረ ለመረዳት አንድ “Traditional Ethiopian Scholarship” የተሰኘ “የያሁ ግሩፕ” አቁሜ ከተወሰኑ ወዳጆች ጋራ ርስ በርስ ስንማማር ቆይተናል።

Wednesday, April 10, 2013

ረ ኡ ኡ! ግፍ በዛ! እጅግ፥ እጅግ፥ እጅግ በዛ!!!

"የቅ/ሥላሴ መን/ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ቀሚሳቸውን አንጥፈው ሲለምኑ ዋሉ" ምን እየተሠራ ነው?

በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተምሬኣለኍ፤ አስተምሬማለኍ። ስማርም ሳስተምርም በነበርኹበት ጊዜ ብዙ ግፍ አይቻለኍ። ግፉ እየባሰ እንጂ እየቀነሰ ሲኼድ አይታይም።አኹን በተማሮቹ ላይ እየደረሰ ስላለው ነገር እያዘንኍ ከምሰማ በቀር እኔ ምንም መረጃ መጨመር አልችልም። ግን አንድ የቆየ ትዝብቴን ባካፍላችኍ እዚያ አካባቢ ያለውን ኹናቴ በጉልህ ያሳያችኍ ይኾናል።

Sunday, April 7, 2013

የደብረ ዘይት ትዝታ!

ታዋቂው ጥንታዊ ፈላስፋ አርስጣጣለስ ሰው በተፈጥሮው ፖለቲከኛ እንስሳ (political animal) ነው ይላል። ያርስጣጣለስ “ወልዱ ዋሕድ ወእሩዩ” (አንድያ እና እኩያ ልጁ፦ the only begotten and co-equal son) እንደኾነ የተነገረለት ዘመናዊ ፈላስፋ ሄግል፤ የሰውን ተፈጥሮኣዊ ፖለቲከኝነት ሲያጦዘው፤ ሰው ኹሉ ካንድ ጠቅላይ መንፈስ (absoluter Geist) ሱታፌ ያለው እንደኾነ አድርጎ አስቀምጦታል።

Wednesday, February 13, 2013

ማብራሪያ

እንደ ኢትዮጵያውያን፥ እንደ ተዋሕዶ ልጆች አኹን የምንገኝበት ዐጸብጺብ (የጭንቅ ጭንቅ) አስገድዶኝ፤ ላፍናቸው ብሻም ባለመቻሌ ሰሞኑን ካንደበቴ የወጡ ኹለት ኀይለ ቃሎች እሊህ ናቸው፦ 

Monday, February 11, 2013

ለነ አባ እንቶኔ


እመሰ አማን ጽድቀ ትነቡ...
ይድረስ ለነ አባ እንቶኔ፦

“ሰላም ለክሙ” እንዳልላችኍ፤ እንደ እኔ ያለ አንድ ምስኪን እንደ እናንተ ላሉ ታላላቆች ከታች ወደላይ ሰላምታ ማቅረብ የማይገባው መስሎ ስለሚታያችኍ፤ ላስቀይማችኍ አልሻምና ይቅርብኝ። “ሰላምክሙ ይብጽሐኒ” ብየ እንዳልማጠናችኍም፤ ስንኳን ለሌላ የሚተርፍ ለራሳችኍ የሚበቃ ሰላም እንደሌላችኍ እያየኍ የሌላችኍን ነገር በመለመን እንዳሳቅቃችኍ ኅሊናየ አይፈቅድልኝም። ስለዚህ የሰላምታን ነገር በዚሁ እንለፈው።    

ሰላምታውን በዚሁ ካለፍነው ዘንድ ነገሬን በቀጥታ ልጀምር። ከቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ ባገኘኹት ላይ ተመርጉዤ። በሊቃውንት ቋንቋ እንድገልጠው ከፈቀዳችኹልኝ፦ ጳጳሳት አይደላችኍ? ከብሉይ ታሪክ ምሳሌ አምጥቼ ግሥ ልገሥሥላችኍ ነው።

Saturday, February 9, 2013

ለማኅበረ ቅዱሳን አባላት

 
በውድ አገራችን ኢትዮጵያ እንዲሁም በመላው ዓለም ለምትኖሩ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት  ﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽ished fact. peakers wele Station  there by ease check your emails before 0600 s. Here it is:tablished fact. peakers we
በያላችኹበት

ሰላመ እግዚአብሔር የሀሉ ምስሌክሙ።

የወቅቱ የቤተ ክርስቲያናችን ዐይነተኛ ችግር ምን እንደኾነ ከደቂቅ እስከልሒቅ ኹሉ ያውቀዋል። የመፍትሔውም አግጣጫ ላይ ብዙ ግርታ የለም።

ይኹን እንጂ ኹናቴውን የተወሳሰበ አስመስሎ ከማሳየት ባሻገር ችግሩን አባብሶ ቤተ ክርስቲያኗን ማጥፋት የሚፈልጉ ኀይሎች አስተማማኝ መፍትሔ ለመሻት የሚደረገውን ጥረት እያደናቀፉ ናቸው። በጉልበት እና በተንኮል።

ማኅበራችኍ እንደ ማኅበር፤ የሊኽን የጥፋት ኀይሎች ጉልበት ፈርቶ የሚገባውን ነገር ከማድረግ ወደዃላ ማለት ብቻ ሳይኾን፤ ለተንኮላቸው እጅ ሰጥቶ በጥፋት ሥራቸው በተግባር እየተባበረ ይገኛል። ምስክር፦
ቤተ ክርስቲያናችንን (ራሱ ማኅበሩ አስፈላጊነቱን አምኖበት ተግባራዊ እንዲኾን እሠራለኍ ሲለን የነበረውን) የዕርቅ ኺደት የጀመሩትን ገባርያነ ሰላም “እንዲሰቀሉ” ሳይቀር ለሚጠይቁ ኀይሎች ሊያሻሽጥ ለየካቲት ማርያም ቀጠሮ መያዙን ነግሮናል።    
ከዚህና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያየናቸው ካሉት መሰል ተግባራቱ በመነሣት እያዘንን እንደምንረዳው፦ ማኀበራችኍ በቅቶታል፤ ክዷል!!!

ማኅበራችኍ ክዷልና፦ ብትችሉ ታደጉት፤ ባትችሉ ለማኅበር ሳይኾን ለእምነታችኍ መቆማችኍን የሚያረጋግጥ ሥራ በመሥራት ራሳችኹን አውጡ። ፍርድ የሚመጣ እየራስ ነውና። 

"እኍኒ ኢያድኅን እኅዋሁ ወኢያድኅን ሰብእ!"
 

በቀናች የተዋሕዶ ሃይማኖት ወንድማችኍ
ፍሥሓ ታደሰ ፈለቀ


Monday, January 14, 2013

Neutralizing the Church...

የቀበረ ሲያረዳ የነበረ ሲያወራ ያምራል! ያምራልና እስኪ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ የሚሉትን ሰምተን እናስተውልስተውል በጥብዐት ተነሥተን ቤተ ክሲያናችንን ነጻ እናውጣአለያም በሰማዕትነት እንለፍ። ይኽ ካልተቻለን ደግሞ ዐርፈን እንቀመጥ እንጂ ባካችን "እገሌ መስቀል ተሳልሟል፤ እገሌ ቆርቧል" እያልን ራሳችን ነኹልለን ሰው ከማነኹለል እንቆጠብ።

...
The TPLF therefore took a series of coordinated steps to neutralize the church’s influence.

Thursday, January 10, 2013

ግፍ ገዘፈ!

በብዙ መንገድ እንደምናየው፦ ግፍ ገዘፈ! ግፍ ሲገዝፍ በግእዝ "ህላዌ ግፍዕ" ይባላል። የኛ ህላዌ፥ የኛ ኑሮ እንዲያ ኹኖ መቅረቱ ነውን--ግዙፍ ግፍ? ይኹን እንጂ፥ ይኹንና ፦ ለኛ ግን ያባታችን የሄኖክን ቃል መስማት ይሻለናል። 
ወእነግረክሙ ፍቁራን፦ አፍቅርዋ ለርትዕ ወባቲ ሑሩ። ወኢትቅረቡ ኀበ ርትዕ በክልኤ ልብ ወኢትኅበሩ ምስለ እለ በክልኤ ልብ። አላ ሑሩ በጽድቅ ደቂቅየ። ወይእቲ ትመርሐክሙ በፍናዋት ኄራት። ወጽድቅ ይከውን ለክሙ ሱታፌ። እስመ አአምር ከመ ይጸንዕ ህላዌ ግፍዕ ወትትፌጸም መቅሠፍት ዐቢይ ዲበ ምድር። ወትትፌጸም ኩላ ዐመፃ ወትትገዘም እምሥረዊሃ። ወኩሉ ሕንፃ የኀልፍ...
ወዳጆቼ እነግራችዃለኊ፦ፍትሕ-ርትዕን/ሕግን ውደዷት በሷም ኺዱ። ኹለት ልብ ኹናችኊ ወደሕግ አትቅረቡ፤ ኹለት ልብ ከኾኑም ጋራ አትተባበሩ። በጽድቅ/በእውነት ኺዱ እንጂ፤ ልጆቼ። ርሷም በቀና መንገድ ትመራችዃለች።  ጽድቅም ድጋፍ ይኾናችዃል። የግፍ ሥራ እንዲገዝፍ፥ እንዲጸና፤ በመጽናቱም በምድር ላይ ታላቅ መቅሠፍት እንዲፈጸም አውቃለኊና። ዐመፃ ኹላ ከሥሯ ተቆርጣ ትጠፋለች። ሕንፃም ኹሉ ያልፋል... 
ዘተወክፈ ነቢየ በስመ ነቢይ ዐስበ ነቢይ ወእሴተ ነቢይ ይነሥእ ወይረክብ እምኀበ እግዚአብሔር አምላኩ!
ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢዩን ዋጋ የነቢዩን በረከት ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል!

Thursday, January 3, 2013

Thoughts on the Primeval Language

"And the whole earth was of one language--[i.e., Geez/Ethiopic]-- and of one speech" (Gen. 11:1).  It seems so, for the word "Geez" literally means "First, Primeval" and certain features of its grammar indicate that it is... 
to be continued

Wednesday, January 2, 2013

ሕዝቡም፥ ካህኑም፥ ሊቃውንቱም፥ ኹሉም ላንድነት ሐሳብ መሰንዘር አለበት! (የቀጠለ)

"በዚህኛውም ሲኖዶስ በዚያኛውም ሲኖዶስ በኲል... ሕዝባቸውን... ካህናቱን ቢያሳትፉ!... የሃይማኖት ልዩነት አልተፈጠረ፥ ሕፀፅ አልተፈጠረ፤ ከኹለቱም በኲል እውነተኛው ኦርቶዶክሳዊ ሥርዐት ነው እየተካኼደ ያለው... ማሰብ አለብን።... ካልኾነም ደግሞ ከበታች ያለው በሚያገኘው አጋጣሚ ላባቶች ዐሳብ ማቅረብ አለበት።... ኹሉም በሚችለው፥ ሕዝቡም፥ ካህኑም፥ ሊቃውንቱም፥ ኹሉም እንደው ላንድነት ሐሳብ መሰንዘር አለበት፤ ማቅረብ አለበት።ያንን ደግሞ አባቶች የመቀበልና... ከነሱ'ንኳ የተሰወረ ነገር ቢኖር በሕዝቡ ተገልጦ ከመጣ መቀበል አለባቸው።"   "ለመሾሙ መቸኮል የለበትም። በዐቃቤ መንበር እየተጠበቀች ለምን--ሲኾን አይወስድም--ለምን ዓመታት አይወስድም ይኸን መልካም ነገር ለማምጣት። እና የማንም ተጽእኖም፥ ምንም የሚባል እንዲያው ከቤተ ክርስቲያኗ ዓላማ ውጭ የኾነ ዓላማ መጥቶ እንዳያደናቅፋቸው አባቶቻችን ጥንቃቄ አድርገው ለጊዜያዊ ሕይወታቸው ሳይኾን ለሚመጣ ታሪካቸው ማሰብ አለባቸው!... እና እግዚአብሔር አምላክ የሰላም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላሙን ባባቶቻችን ላይ አድሮ እንዲያመጣልን ደግሞ  የእሱ የተቀደሰ ፈቃዱ ይኹንልን። አሜን።"

ባካችኹ ለአበው ሊቃነ ጳጳሳት አሰሟቸው!


ዂላችንም አንድነት የምትለዋን ታላቅ ቃል መከተል አለብን!


"ምናልባት እነሱን ታሪክ ይፋረዳቸው እንደኾነ ነው'ንጂ እግዚአብሔር ከፈቀደ በሌላም መልክ አንድነቱ ሊመጣ ይችል ይኾናል።በፈቀደበት ቀን። እና ግን ይኸ ታሪክ የኛው እንዲኾን ያባቶቻችን --ያኹኖቹ አባቶቻችን--እንዲኾን ዂላችንም አንድነት የምትለዋን ቃል መከተል አለብን"

ባገር ውስጥ ያላችኊ ወዳጆቻችን ባካችኊ 
እንደምንም ብላችኊ ይህንንና ቀጣዩን መልእክት 
ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዲሰሙት አድርጉልን!አዎ ባገር ውስጥም ካገር ውጭም ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት 
መልአከ ሕይወት ሐረገ ወይን ብርሃኑን በደንብ ያውቋቸዋል
በሙያቸውና በመልካም ምግባራቸውም ያከብሯቸዋል ብለን እናምናለን
ታዲያ አኹን ምናለ "እንዘ ወልድየ ኩነኒ አበ" ያለውን አስታውሰው 
የቡዙ ልጆቻቸውን ዐሳብ የሚወክለውን የሊህን ሊቅ ድምፅ ቢሰሙ? 
ምእረ!
[አንድ ጊዜ!]