Saturday, October 8, 2016

“ቤተ ኢትዮጵያ”ን ስለመገንባት

  1. አጭር የታሪክ ማስታወሻ  

ተወደደም ተጠላም፤ እስካኹን ባገራችን ሰፍኖ ያለው “ገዡ መንፈስ” የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ነው። የተቀረው አንድም ተፎካካሪ ወይም አኩራፊ አለያም ተፃራሪ ነው፤ ኢትዮጵያዊነትን።

Saturday, February 6, 2016

ለእመቦ እዝን ሰማኢ ዘቦ

በብሉይ፣ በሐዲስ ስለተመሠረተው ኢትዮጵያዊ ሥርዐተ-አምልኮ

በያግጣጫው ጩኸት! በምክንያትም ያለምክንያትም መደናቆር! እስከ ማእዜኑ/እስከ መቼ?
(ለእመቦ እዝን ሰማኢ ዘቦ = ምናልባት ሰሚ ጆሮ ያለው ቢገኝ፦ ድንቁ የቅኔ ፈጣሪ፣ የትርጓሜ ሊቅ /ብርሃን አድማሱ  ጀንበሬ በቅኔ መነሻነት ያሉትን እንስማ እስኪ፦)
………………………………………………………………………………………
ይህም በየቀኑ እንግዳ እንግዳ ድርሰት እየደረሱ ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ በብሉይ በሐዲስ የታዛዘ ነው እንጂ፤ ልብ ወለድ ነገር አይደለም። ከምን ይገኛል ቢሉ?

Wednesday, January 6, 2016

እንቋዕ አብጽሐክሙ

ናሁኬ ፈለሰት በረከተ እግዚአብሔር ኀበ ቤተ ዳዊት...  ወእምዘርዐ ዚኣሁ አንሥአ ለነ እግዚአብሔር ቀርነ መድኀኒትነ። ወዓዲ ኢቦአ ውስተ አዕጻዳቲሆሙ ለነገሥተ ገሊላ። ኢኀረያ ለወለተ ሄሮድስ። ወለተ ነዳያን ኀረየ እምወለተ ዐበይቶሙ ለነገሥተ ይሁዳ። እንዘ እግዚአብሔር ውእቱ ውስተ ማሕፀነ ብእሲት ኀደረ።...
እነሆ የእግዚአብሔር በረከት ወደዳዊት ቤት ገባች... ከዘሩም እግዚአብሔር የድኅነታችንን ቀርን [ሊያድነን ሥልጣን ያለው ክርስቶስን] አስነሣልን።

Monday, December 28, 2015

Of Western Scholars

Scholars vs. Looters 
There is no denying the fact that there have always been pillagers, some as mean as the devil and some as cunning as Jacob. Ethiopia knows both kinds, indeed. But we need to distinguish. True scholars are as far removed from malicious looters, as is the east from the west!

Friday, December 18, 2015

On Prof. Getatchew Haile

[An excerpt from a paper presented to]
The XV International Conference of Ethiopian Studies
Hamburg University, 21-25 July 2003
The Intellectual Legacy of the Ethiopian Church
A Philosophico-Hermeneutical Reappraisal  of “Andəmta”
 Fisseha Tadesse Feleke 
....................................................................................................................................

Getatchew Haile’s Phenomenal Insights and his “Bahrä Hasab”

What makes Getatchew’s insights phenomenal? Few points may help visualise. For Getatchew, “The origin of Ethiopian Studies is naturally in Ethiopia and in the works of Ethiopian writers.”[1]Being the first to teach in Amharic at AAU, his proposal to establish a chair for Qene[2] there—even if it seems to have been totally forgotten—bears witness of his aspiration for intellectual development rooted in tradition. Needless to say, what would have been done with the EMML, if not for those brilliantly compiled catalogues of his, and the editions and commentaries he has published?[3]

Wednesday, December 2, 2015

ዜና ሠናይ!

የቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ በስፋቱና በጥልቀቱ በሰሜን አሜሪካ የመጀመሪያ የሚኾን የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ሊከፍት መኾኑን ስንሰማ እጅግ ተደሳን (ደስ አለን)!!! ውጤቱ እንዲሠምር ታዲያ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይገባል።

https://slate.adobe.com/cp/ODPLq/

ቶሮንቶኣውያን Bikila Award ለቅዳሜ ታኅሣሥ 9 (December 19) ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ተገኝታችኍ ድጋፋችኍን እንድትሰጡ ይኹን። አደራ!

ለዚህ ጥናትና ምርምር ማዕከል መከፈት ቁልፍ ሚና የተጫወቱት ታላቅ ምሁር ፕሮፌሶር ማይክል ጀርቨርስ ይባላሉ። መዝገበ ሥዕላት የተሰኘ ድረ ገጽ አላቸው፤ ይጎብኙት፦

http://ethiopia.deeds.utoronto.ca/

Wednesday, October 22, 2014

ለማኅበረ ቅዱሳን

እናንተ ፍዝ ኾናችኍ
ሌላውንም እያፈዘዛችኍ
እንቀጥላለን ካላችኍ

ስሙኝ ወንድሞቼ ልንገራችኍ፦

እግዜር ባይጭክንም ሊርቃችኍ
አይነሣምና ሊረዳችኍ

ድንገት ሳይፈታ ጽናታችኍ
ንቁ እና አዘንብሉ ቆርጣችኍ
ወደ ቀናው መንገድ ባካችኍ


"እምቅድመ ትጽንን ኅሊናሁ ለሰብእ ለኂሩት ወለእከይ፤ ኢትረድኦ ወኢትርሕቅ እምኔሁ።"
(የሰው ኅሊናው ወይ ወደ በጎ፥ ወይ ወደ ክፉ ሳይጸን (ሳያዘነብል) በመካከል ሳለ--ማለትም ፈዞ ሳለ--አትረዳውም፥ አትርቀውም።)

በቀናች የተዋሕዶ ሃይማኖት ወንድማችኍ!